ለሳምንቱ የተመረጡ መዝሙሮች  2-21-2016
MEZMURE for the weekend  2-21-2016
ለሳምንቱ የተመረጡ መዝሙሮች 2-28-2016
MEZMURE for the weekend 2-28-2016

The gadget you added is not valid

የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን 
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን (2)


እመቤታችን-----ለእኛ ምርኩዝ ነሽ---------ከለላም ሆንሽን
…………… የእሳት ሙዳይ ------------እሳትን ታቀፍሽ 
…………… በብርሃን ተከበሽ ---------- ወርቅ ለብሰሽ 
…………… ከሴቶች ሁሉ ---------- አብ መረጠሽ
…….አዝ…..
……………. ድንግል ሆይ ልጆችሽ -----ዘወትር ይጠሩሻል
……………. ስምሽን ለልጅ ልጅ -----ያሳስቡልሻል 
……………. በተሰጠሽ ፀጋ ------ባማላጅነትሽ 
……………. ምሕረትን አሰጭን ------ከመሐሪው ልጅሽ 
…….አዝ…..
……………. ያልታረሰች እርሻ -------ዘር ያልተዘራባት
……………. የሕይወትን ፍሬ --------ሰጠችን የእኛ እናት 
……………. የታረደው መሲሕ ------እናቱን ወደዳት
…………….. በቀኙ ቆማለች -------ድንግል እመቤት ናት 
…….አዝ…..
……………. የእውነት ደመና ------ዝናብ የታየባት
…………… ወዳናለች ድንግል ----- የታተመች ገነት
…………… ክብርት ለሆነችው ----- ኑ እንዘምርላት
…………… ደስ ይበልሽ እንበል -- ለብርሃን እናት፤በልዎ  ለእግዚአብሔር  ግሩም  ግብርከ /2/
እግዚአብሔርን በሉት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው /2/
ቀላያትን በእልፍኝ የምትለካቸው
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ተራሮችን በእጅህ የምሰፍራቸው
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ቃልን ብቻ ልከህ የምታሰማምር
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ለድንቅ አጠራርህ ግሩም ነህ እግዚአብሔር
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
በልዎ  ለእግዚአብሔር  ግሩም  ግብርከ /2/
እግዚአብሔርን በሉት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው /2/
ስለ ሓጢያቴ ብዛት ሊወግሩኝ ሲነሱ
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ከፊቱ አቁመውኝ ሊከሱኝ በብዙ
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ጥፋቴን አይሻም እርሱ መች ፈረደ
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ውለታው ብዙ ነው ሊምረኝ ወደደ
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
በልዎ  ለእግዚአብሔር  ግሩም  ግብርከ /2/
እግዚአብሔርን በሉት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው /2/
እሰግድልሃለው ፊትህ ተንበርክኬ
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ውለታህ ማርኮኛል  እግዚአብሔር  አምላኬ
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
ካንተ ጋራ ሆኜ ምን ይጎልብኛል
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
በምረትህ ጎብኘኝ ፀጋህ ይበቃኛል
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው
በልዎ  ለእግዚአብሔር  ግሩም  ግብርከ /2/
እግዚአብሔርን በሉት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው /2/